Kebbede Mikael’s biography, net worth, fact, career, awards and life story

Intro Ethiopian writer (1915-1998)
Was Writer 
From Ethiopia 
Type Literature 
Gender male
Birth 1915
Death November 1998
(aged 83 years)

ከበደ ሚካኤል (1909-1991) በደብረ ብርሃን ከተማ፣ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም.ተወለዱ። ወደ አዲስ አበባ እንደ መጡ መጀመሪያ በአሊአንስ ኢቲዮ-ፍራንሴዝ በኋላም በላዛሪስት ሚሲዮን ትምህርታቸውን ተከታተሉ። የሼክስፒርን ሮሜዎና ዡልየትን ማክቤዝን በመተርጎም እውቅናን ለማትረፍ ችለዋል።

ሌሎች ታዋቂ የትርጉም ሰራዎች መሃል፦

  • ከይቅርታ በላይ በሚል አርእስት ከBeyond the Pardon በ M.Clay የተተረጎመው ሊጠቀስ የቻላል።

ከበደ ሚካኤል 30 ገደማ መፃሕፍትን ፅፈዋል። ከበደ ሚካእል ካበረከቷቸው የቴአትር ስራዎች

  • የትንቢት ቀጠሮ
  • የቅጣት ማእበል
  • ካሌብ
  • ሃኒባል

ይገኙባቸዋል።

ከበደ ሚካኤል በርካታ የስነ ጽሁፍ ስራዎች ባለቤት በመሆናቸው በተለይም ለልጆች ትምህርት አዘል ጽሁፎችን የግጥም የፈጠራ ስራዎችን ቅኔዎችን በስፋት በማበርክታቸው በኢትዮጵያ የስነጽሁፍ መድረክ ገናና ከሆኑት ደራሲዎች አንዱ ናቸው። ከነዚህም መሃል፦

  • ታሪክና ምሳሌ ፩
    • ታሪክና ምሳሌ ፪
  • የህሊና ብርሃን
  • የቅኔ ውበት (በ ……… ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
  • ጃፓን እንዴት ስለጠነች (በ ……. ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
  • ታላላቅ ሰዎች (በ …….. ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)
  • የሥልጣኔ አየር (በ ……… ዓ.ም. ታተመ/ተጻፈ።)

ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የሰዎች ስነ ምግባር ላይ የማተኮርና ምክር አዘል መልእክቶችን የማስተላለፍ ዝንባሌአቸው በአብዛኛው ስራቸው ላይ ይንጸባረቃል።

ዘመናዊት ኢትዮጵያን ለማደርጀት በተደረገው ትግል በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ እኒህ ፈላስማ፥ ባለቅኔ፥ ጸሐፌ-ተውኔት፥ ደራሲና አንጋፋ ጋዜጠኛ ፥ ‘የቀለም ሰው’ በሀገራችን የመጀመሪያ የነበረውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት በቀዳሚነት የተቀበሉ ሲሆን፣ አዲስ ትውልድ ላፈራ ስብእናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክቶሬት ዲግሪ ሸልሟቸዋል። በተረፈም ከፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሶቭየት ህብረትና ሜክሲኮ ሽልማትን ተቀብለዋል።

በተረፈ የትምህርት ሚኒስትር ዳይረክተር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተከታይ ዳይሬክተር (፲፱፵፪)፣ የብሄራዊ መጻህፍት ቤት ዳይረክተር (፲፱፵፬)ና የካቢኔ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል።

ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል፥ ኢትዮጵያዊ ‘የቀለም ሰው’ ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. በሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።

ናሙና ግጥሞች


የተማረ ሆኖ እውነቱን የማይገልጽ ፣
ባለ ጸጋ ሆኖ ገንዘቡን የማይሰጥ፣
ደሃ ሆኖ መስራት የማይሻ ልቡ፣
ሶስቱም ፍሬ ቢሶች፣
ለምንም አይረቡ።

አይነ የለውም አሉ የሰነፍ ልመና
ወደ አምላክ ሲጸልይ ማታ በልቦና
መንገዱ ሳይመታኝ ባቧራ በጭቃ
አድርገኝ ይለዋል ላገሬ እንድበቃ
እንጦጦ ተኝቼ ሃረር እንድነቃ

መርዝም መድሃኒት ነው ሲሆን በጠብታ
እንዲሁም ለተንኮል አለው ቦታ ቦታ
ምን ቢሰለጥኑ ቢራቀቁ በጣም
ሁልጊዜ ደጋግሞ ብልጠት አያዋጣም።
በጅ የተበተቡት ተንኮል ዞሮ ዞሮ
ማጋለጡ አይቀር እጅና እግር አስሮ ።
መጽሓፉም ይለናል ሲያስተምረን ጥበብ
ብልጥ ሁን እንደባብ የዋህ ሁን እንደርግብ
ስለዚህ በብልጠት ተንኮል ስትሰሩ
በዝቶ እንዳይገላችሁ ገርነት ጨምሩ …
ከየዕውቀት ብልጭታ የተወሰደ

ዋቢ ምንጮች

[1]
You May Also Like

Jonathan Demme’s net worth, biography, fact, career, awards and life story

Jonathan Demme Net Worth: Jonathan Demme was an American filmmaker, writer and director who had a net worth of $40 million dollars. Ted Demme was famous for directing movies like “Blow”, “The Ref” and “Who’s The Man”. He was born in Nassau County, New York, in 1944. Jonathan Demme began his film industry career in the early ’70s with “The Hot Box” and “Angels Hard as They Come”. He directed several films, including “Crazy Mama” and “Melvin and Howard”, before landing Kurt Russell and Goldie Hawn for a production of “Swing Shift”. The movie flopped, and Demme took a break from Hollywood until he returned with a bang in 1991 with “The Silence of the Lambs”. He took home a Best Director Oscar for the movie and was nominated for two BAFTA awards and a Golden Globe. Demme went on to work on “Beloved”, “Philadelphia”, “The Truth About Charlie”, “The Manchurian Candidate”, “Man from Plains” and “Rachel Getting Married”. Demme produced several music videos, including Bruce Springsteen’s 1995 hit “Murder Incorporated”. He also directed the Talking Heads’ documentary film “Stop Making Sense”. He owned the production company Clinica Estetico and sat on the board at the Jacob Burns Film Center in New York, where he puts together a monthly series known as “Rarely Seen Cinema”. The University of Florida alum was married twice and had three children: Ramona, Brooklyn, and Josephine. He received an honorary doctorate from Oberlin during the school’s 2013 graduation. Unfortunately, Jonathan Demme died on April 26, 2017 at the age of 73. He had been suffering from esophageal cancer and complications from heart disease. He was the uncle of director Ted Demme who died in 2002 at the age of 38.
Read More